Your cart is currently empty!

የአማራ ፋኖ በሸዋ ከሰም ክ/ጦር ነበልባል ብርጌድ ዘመቻ አንድነት በተሳካ እየፈፀመ ይገኛል።
ከ5 ሻለቃ የተውጣጣው በአንድነት ዘመቻ አንድነት ለማሳካት ያነሳሳው እንደ ምክንያት በእንቡር አካባቢ ብሄር ተኮር ጥቃት የአገዛዙ ሰራዊት እየፈፀመ እንደሆነ ሲሰማ የነበልባል ብርጌድ አዛዦች የጦር ኣዛዡ አምሳለቃ ፍቃዱ እና የአስተዳደር ሃላፊው በላይሁን አድማሱ ጦራቸው ሸክፈው እንደየአከባቢው የሻለቃዎቹ ለግዳጅ የተጠሩበት ርቀት ግዳጁን ለመፈፀም ከሶስት ቀናት በላይ ተጉዟል።
ጦሩ ሲጋዝ በየአከባቢው የሚገኘው የአገዛዙ ሰራዊት መጥቡኝ እያለ ሲፈረጥጥ ለመታዘብ በቅተናል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ረጅሙንና ሰንሰለታማ የነበልባል ብርጌድ ጉዞ ተራራው ፣ ሸለቆው ፣ ረባዳው ፣ ሙቀቱና ቁሩ እየተፈራረቀባቸው ሲጋዙ በእግር የሚሄዱ ሳይሆን ተሽከርካሪ ጎማ የተገጠመላቸው ይመስላሉ።
በዚህ ግዳጅ ላይ ከቃኝ ማሃንዲስ ተጨማሪ የህክምና ቡዱኑን ፣ የብርጌዲ የመሳርያ ጥገና ክፍል እና የሚድያ ክፍል ተሳትፈውበታል።
በመጨረሻ ተናዳፊዎቹ የነበልባል አናብስቶቹ ወገን ፍለጋ ሲዋትቱ የነበሩት የተገፉት የአማራ ህዝቦች ሲደርስ እናቶች ፊታቸው የሚታየው ደስታ ብቻ ሳይሆን ተመስገን የሚሉ በየአቅጣጫው ተመልክተናል አባቶችና ወጣቶችም በጭፈራ “ነበልባል መጣ ነፂ ሊያወጣ ” እያሉ ደስታቸው ሲገልፁ ነበር።
የነበልባል አናብስቶቹ አስፈላጊው እረፍት ከወሰደ በሃላ ለግዳጅ ዝግጁ እንዲሆን በአምሳ አለቃ ፍቃዱና በበላይሃን አድማሱ አስፈላጊውን ምክርና የሚፈፀመው ግዳጅ የት እንደሆነ ግልፅ ተደረገ ጦሩም በእልልታ ግዳጁ ተቀበለ።
ግዳጁ ለመጀመር ቃኝዎችና የተወሰኑ የሌላ ሻለቃዎችና መሃንዲሶች የሚመሩ ተመረጡ አመራሮቹም ከአጃቢዎቻቸው ከፊት እየመሩ ጠላት ምሽግ ይዞት የነበረው በእንቡር ከተማ ዙርያ በጦር አዛዡ አምሳለቃ ፍቃዱ ጥላሁን ከልክሌ እና በአስተዳደር ሃላፊ በላይሁን አድማሱ በሁለት አቅጣጫ መጠጋት ሲጀምሩ ጠላት በቅርብ ርቀት በመነፀር ሲከታተል የቆየው የነበልባል ሙሉ ሃይል ገና ወደ ግዳጁ ሳይቀላቀል ጠላት እግሬ አውጪኝ በማለት ፈርጥጦ ወደ እንቡር ከተማ ገብቷል የነበልባል ብርጌድ ከአከባቢው የፋኖ አባላት በዚህ ሰአት የጠላት ምሽግ ተቆጣጥሯል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ይህ የሰማው የአገዛዙ ሰራዊት እገዛ እንዲያደርግ ጥሪ አድርጎ በሁለት ኦራል ሲመጣ የነበረው የኛወቹ የነበልባል ተናዳፊዎቹ ቦታ ይዘው በመቆየት አንዱ ኦራል ላይ ምላጫቸው በተሳካ ቦታ በማሳረፍ ተጭኖ ሲመጣ የነበረው እንዶድ በሚባል ወንዝ ሙትና ቁስለኛ ሆኖ ተደናግጦ ተመልሷል።
ሙሉ ዘገባው እየተከታተን እናቀርባለን።
ክብርና ሞገስ ለትግሉ ሰማእታት
ድል ለአማራ ፋኖ
አማራ ፋኖ በሸዋ ከሰም ክ/ጦር
Leave a Reply